አማርኛ (Amharic)

አማርኛ ለሚናግሩ ሰዎች የነቀርሳ መረጃ እና ድጋፍ  

(Cancer information and support for people who speak Amharic)

ነቀርሳ ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ከባድ ነው፣ ነገር ግን እርስዎ ብቻዎን አይደሉም። እኛ እዚህ ያለነው እርስዎን ለመርዳት ነው። 

ማንኛውም ሰው፣ ቤተሰብን፣ ጓደኞችን እና ተንከባካቢዎችን ጨምሮ፣ ስለ ነቀርሳ፣ መከላከያ፣ ክምና እና የድጋፍ አገልግሎት፣ ሊያነጋግሩን ይችላሉ። 

Cancer Council Victoria እርስዎን ለመርዳት እዚህ ብዙ የነጻ ድጋፍ አገልግሎቶች አሉት በተጨማሪም በቪክቶሪያ በማንኛውም ቦታ ለእርስዎ ተስማሚ ከሆኑ ሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች ጋር እንዲገናኙ መርዳት እንችላለን ምን ዓይነት አገልግሎቶች እንዳሉ ካላወ ምንም ችግር የለውም፣ ለመርዳት ነገሮችን ልንጠቁም እንችላለን። 

እኛ ልንረዳዎት የምንችለው: 

 

መረጃ በአማርኛ ቋንቋ 

በገጹ የላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያለውን የተደራሽነት መሣሪያ አሞሌ በመጠቀም እና ቋንቋዎን በመምረጥ በአብዛኛዎቹ የማህበረሰብ ቋንቋዎች ትርጉሞችን ማንበብ ወይም ማዳመጥ ይችላሉ። በተጨማሪም መሣሪያው የማየት ወይም የመስማት ችግር ያለባቸውን ወይም የመማር ችግር ያለባቸውን ሰዎች መርዳት ይችላል። 

እንዲሁም ከዚህ በታች ባለው ሰንጠርዥ በNAATI ተቀባይነት ባላቸው ባለሙያዎች የተተረጎሙ መገልገያዎች ትርጉሞች ኣሉን 

እኛን ለማነጋገር በአማርኛ ቋንቋ 

እኛን ለማነጋገር 

  • በማህበራዊ መዲያ መልእክት ይላኩልን  

  • በኢሜል ይላኩልን 

  • በስልክ ይደውሉልን። 

ማንኛውም ሰው እኛን ማነጋገር ይችላል፤ ይህም ጓደኞችና የቤተሰብ አባልን ያካተተ። ይህ ያለክፍያ በነጻና ሚስጢራዊነት ባለው ነው። 

በእንግሊዝኛ ለመናገር በስልክ 13 11 20 መደወል። 

አስተርጓሚ ተጠቅመው በአማርኛ እኛን ለማነጋገር 13 14 50 ይደውሉ። 

ስልክ በሚደውሉበት ጊዜ የእርስዎን ቋንቋ ስም መናገር እና ከዚያም ወደ Cancer Council በስልክ 13 11 20 ለመደወል አስተርጓሚን መጠየቅ።   

በግለሰብ ላይ ክምና ምክር መስጠት አንችልም። 

ለነቀርሳ መረጃና መገልገያዎች

(Cancer Information and Resources)

የሚከተሉት መረጃዎች እውቅና ባለው NAATI ባለሙያ ተርጓሚዎች የተተርጉመ ነው። እባክህ እነዚህን መገናኛ መርበቦች ለጓደኞችዎና ለቤተሰብዎ ለማካፈል ነጻነት ይሰማዎት።

የሚፈልጉት መረጃ እዚህ ከሌለ፤ እባክዎ ለእርዳታ እኛን ያነጋግሩ

በተጨማሪም ቀለል ባለ ቋንቋ ወይም Easy Read ላይ የሚገኘውን መገልገያ መረጃ ተጨኖ ማውጣት ይችላሉ እነዚህ የአካል ጉዳተኞች፣ ድሜ አንጋፋ የሆኑ ወይም ማንበብና መጻፍ ድጋፍ ለ ሚያስፈልጋቸው ሰዎች ተስማሚ ይሆናል

አማርኛ

English equivalents 

የሚከተለው የድጋፍ አገልግሎት ሊጠቅማቸው ይችላል The following support services may assist you